ሪፖርት| ሄለን እሸቱ ደምቃ በዋለችበት ጨዋታ መከላከያ የሊጎ መሪ መሆን ችሎል።

Wed 11 Dec 2019 Dawit Habet

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ 8:000 በአ.አ ስታዲየም የአንድ ከተማ ክለቦች አገናኝቷል በሄለን እሸቱ ሦስት ጎሎች ታግዞ መከላከያ አዲስ አበባንሽ3-0 አሸንፏል።ከጅምሩ ጀምሮ ጫና በመፍጠር እረገድ ጥሩ የነበሩት መከላከያዎች ቶሎ ቶሎ ኳሱን ወደፊት ለመጫወት በመሞከር  ተደጋጋሚ የጎል እድል መፍጠር ችለዋል።

አዲስ አበባዎች ምንም ቅንጅት የማይታይበት መልኩ እና ኳሱን ይዘው ከመጫወት ይልቅ ኳሱን ለመከላከያዎች ለቀው ወደ ኃላ ማፈግፈጋቸው ለተጋጣሚያቸው የተሻለ የመጫዎቻ ሜዳ እና በተደጋጋሚ የጎል እድል እንዲፈጠርባቸው አድርጎባቸዋል።አዲስ የተቀላቀልችው አይዳ ዑስማን በተደጋጋሚ ጎል የሚሆኑ ኳሶችን ስታበክን በምትኩ ጥሩ ስትንቀሳቀስ የቁየችው አረጋሽ ካልሳ ግልፅ የማግባት እድል ብታገኝም ሳትጠቅምበት ቀርታለች።
ሙሉ የጫወታ ብልጫ መውሰድ የቻሉት መከላከያዎች ብዙ የጎል እድል ቢፈጥሩም ኳስና መረብ ሳያገናኙ 0-0 በሆነ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ከእረፍት በኃላ የበላይነታቸውን መድገም የቻሉት መከላከያዎች በ53ኛው ደቂቃ ባገኙት መዓዘን ምት የተሻማውን ኳስ ኢልሳቤጥ ብርሃኑ በግንባር የገጨችውን ኳስ የአዲስ አበባ ተጫዋቾች ተረባርበው ቢመልሱትም ሄለን እሸቱ በጥሩ አጨራረስ መከላከያን ቀዳሚ ማድረግ ችላለች በአንድ ደቂቃ ውስጥ እራስዋ ሄለን እሸቱ የቀማችውን ኳስ በፍጥነት ወደ ሳጥን ውስጥ ይዛ በመግባት በድንቅ አጨራረስ ሁለተኛ ጎል ማስቁጠር ችላለች።በተከታታይ ጎል የተቁጠረባቸው አ.አ ከተማዎች ተጨማሪ ጎል እንዳይቁጠርባቸው ወደ ኃላ አፈግፍገው ለመጫወት መወሰናቸውና ለመከላከያዎች የበለጠ አጥቅተው እንዲጫወቱ አርጓቸዋል።በ60ኛ ደቂቃ ላይ የተመታው ኳስ ሳጥን ውስጥ በመነካቱ በእለቱ ዋና ዳኛ በሆነችው አዳነች የፍፁም ቅጣት  በመስጠቷ በእለቱ ምርጥ ብቃቷ ላይ የነበረችው ሄለን እሸቱ ለቡድኖ ሦስተኛውን ለእራስዋ ደሞ ሀትሪክ የሰራችበትን ጎል አስቆጥራለች በዚህም መሰራት ሄለን እሹት የሊጉ የመጀመሪያ ሀትሪክ የሰራች ሆናለች።

በ65ኛ ደቂቃ ላይ ለአዲስ አበባ የመጀመሪያ ሙከራ የሆነችውን አስራት ከሳጥን ውጪ አክርሪ የመታችው ኳስ የጎሉን አግዳሚ ታኳ ውጥቷል ለአዲስ አበባዎች ብቸኛ የጎል ሙከራ ሆና የታየች ነበረች። ሲሳይ ገ/ዋህድ ኤልሳቤት ብራሃኑን ቀይራ በመግባት ለመከላከያዎች ተጨማሪ የማጥቃት ጥንካሪ በመሆን ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ችላለች።ጨዋታውም ሙሉ ክፍለ ጊዜ ጥሩ በነበረው መከላከያ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል ይህንንም ተከትሎ መከላከያ የሊጉ መሪ መሆን ችሏል።


ሁለተኛ ሳምንት

ተጨማሪ

Wed 22 Jan 2020
የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ያግኙ
email