ኢትዮጵያዊቷ ተጫዋች ሎዛ አበራ በአውሮፓ ታሪክ መስራቷን ቀጥላለች።

Wed 11 Dec 2019 Dawit Habet

Image copyrighለማልታው ቢርኪርካራ እግር ኳስ ቡድን የምትጫወተው ኢትዮጵያዊቷ እግር ተጫዋች ሎዛ አበራ ቡድኗ ትናንት ከሂበርኒያንስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሰባት ግቦችን በስሟ ማስመዝገብ ችላለች።ለማልታው ቢርኪርካራ እግር ኳስ ቡድን የምትጫወተው ኢትዮጵያዊቷ እግር ተጫዋች ሎዛ አበራ ቡድኗ ትናንት ከሂበርኒያንስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሰባት ግቦችን በስሟ ማስመዝገብ ችላለች።

ለማልታው ቢርኪርካራ እግር ኳስ ቡድን የምትጫወተው ኢትዮጵያዊቷ እግር ተጫዋች ሎዛ አበራ ቡድኗ ትናንት ከሂበርኒያንስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሰባት ግቦችን በስሟ ማስመዝገብ ችላለች።

ሰባት ልጆች ላፈሩት እናት እና አባቷ አምስተኛ ልጅ የሆነችው ሎዛ ተወልዳ ያደገችው የከንባታ ጠምባሮ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ዱራሜ ነው።

ባደገችበት ሠፈር ካሉ ወንድ እኩዮቿ ጋር እየተጋፋች ኳስን ተጫውታለች። የሎዛ ፕሮፌሽናል ኳስ ተጫዋችነት ጉዞ የተጀመረው የከንባታ ዞንን ወክላ ስትጫወት ባይዋት መልማዮች አማካይነት ነው።

ብዙም ሳትቆይ ሎዛ የሐዋሳ ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ቡድንን ተቀላቀለች። ከሐዋሳ ጋር ዋንጫ ባታነሳም እዚያ በቆየችባቸው ሁለት ተከታታይ ዓመታት የክለቡ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች።

ሐዋሳ ከተማን ከለቀቀች በኋላ በደደቢት አራት ዓመታትን ያሳለፈችው ሎዛ በሁሉም ዓመታት በተከታታይ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ሆናለች ለሶስት ተከታታይ ዓመት ደግሞ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮን ከደደቢት ጋር መሆን ችላለች።

በአሁኑ ሰአት በማልታ ደሴት ከፍተኛ ሊግ ላይ ለሚሳተፈው ቢርኪርካራ የምትጫወተው ሎዛ በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልእክት ''ዛሬ በነበረን ጨዋታ በማልታ ሊግ ላይ በአንድ ጨዋታ ብቻ ሰባት ጎል በማስቆጠር ሌላ ታሪክ መፃፍ እና መስራት ስለቻልኩ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ላይ በአንድ ጨዋታ ብቻ ዘጠኝ ጎል አግብቼ ነበር'' ብላለች።

ሎዛ አበራ በኢሮፓ ዋንጫ ላይ (ቻንፕስሊግ ) በቅርቡ ከቡድኑ ጋር እንደምትሳተፍ ሲገለጽ የመሀል አውሮፓ  ቡድኖች አይናቸውን ወደሷ ይጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ ቢቢሲ


ሁለተኛ ሳምንት

ተጨማሪ

Wed 22 Jan 2020
የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ያግኙ
email