ቅድመ ጨዋታ እይታ | አዲስ አበባ ከተማ ከ መከላከያ

Wed 11 Dec 2019 Dawit Habet

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ከ መከላከያ ነገ 8፡00 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያደርግ ይሆናል።
ባለሜዳው አዲስ አበባ ከተማ ቡድኑ በቅርቡ ከመፍረስ ተርፍ ወደ ዝግጅት በመመለስ ለፌዴሬሽኑ የዝግጅት ጊዜ ስላነሰን የይራዘምለን ደብዳቤ ቢያስገቡም ፌዴሬሽኑ ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ጨዋታቸውን በተያዘላቸው ፕሮግራም መሰረት እንዲያከናውኑ ማሳወቁ የሚታወስ ነው። አ.አ ከተማ በርካታ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ መቀላቀል ችሏል ።የዝግጅት ጊዜ ማነሱ እና ቡድኑ አለመቀናጀቱ የነገው ጨዋታ ፈተና ይሆንበታ ተብሉ ይጠበቃል።

የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች የነበሩትን እነመቤት አዲሱን በክረምቱ ዝውውር ያጡት መከላከያዎች በምትካቸው በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ በመቀላቀል እንደ አዲስ ቡድኑን እየገነቡ ይገኛል። በቅድመ ዝግጅት ጨዋታ ላይ ልዩነት በመፍጠር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያስመለከቱት ከድሬደዋ ከተማ የመጣችው አይድ ዑስማን እና በ2011 እምብዛም የመሰለፍ እድል ያላገኝችው ሲሳይ ገ/ዋህድ በነገው ጨዋታ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ተብለው ይጠበቃሉ። በሌላ ከጥረት ኮርፖሬት እና የቤሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቅ ታሪኳ በርገና ሌላው የቡድኑ ጥንካሬ ትሆናለች ቡድኑ ልምድ ባለቸው ተጫዋቾች መገንባቱ የነገውን ጨዋታውን ይቀልለታል ተብሎ ይጠበቃል።


ሁለተኛ ሳምንት

ተጨማሪ

Wed 22 Jan 2020
የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ያግኙ
email