በእኔ ጊዜ ግን ቤሔራዊ ቡድኑ እያደገ መሄዱ ቡዙ ማረጋገጫ አሉ ። አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ!!

Fri 22 Nov 2019 Dawit Habet

የኢትዮጵያ የሴቶች ቤሔራዊ ቡድን የሴካፋውን ውጤት ይህንን ጠብቀሽ ነበር?

ውጤት ያመጣል ብይ ነበር ከነበረው አንፃር ነገር ግን ይህ እግር ኳስ ነው ሁሌም ፋሲካ የለም ውጤቱ የማይጠበቅም ቢሆንም በኢንተርናሽናል 3 ተጨማሪ ጨዋታዎችን አድርገናል ሰለዚህ ከጨዋታዎቹ የምንማራቸው ብዙ ነገር ይኖራል ብዬ ነው የማስበው።

ከዚህ በፊት ባንቺ በያዝሽውም በሴካፋ የተሻለ የሚባል ውጤት ነበረን አሁን ከምድብ ማለፍ አልቻልንም ከኛ ጋር የነበሩ ደካማ ቡድኑች አሁን በጣም ተሽለው ተገኘተዋል ይህንን እንዴት ታይዋለሽ።

አሰልጣኝ መሰረት ይዛው በሄደችው ቡድንም እኔም ይዥው በሄድኩት ቡድን ይዘውት የመጡት አንድ አሰልጣኝ ናቸው አሁንም አሰልጣኝ ብርሃኑ ይዙት በሄደበትም ቤሔራዊ ቡድኑቹ አሰልጣኞቹ እራሳቸው ናቸው። ሰለዚህ ቡድኑን በማሻሻል በመገምገም እና ወጥ የሆነ ቡድን መገንባት ችለዋል ። የኛ ቡድን በየጊዜው አዲስ አሰልጣኝ አዲስ ተጫዋቾች ሰለሆነ እንዳዲስ ስለምትገነባ እንደዚህ አይነቱ ውጣውረዱ ውስጥ መግባቱ አይቀርም።ሰለዚህ ሌሎቹ ቤሔራዊ ቡድን አራት አመት የተገነባ ቡድን ነው ።ባለፉት ሁለት አመታት ጥሩ ቡድን እየገነባን መጥተን በተለያዩ ውድድሩች ላይ የተሻለ ውጤቶችን ማስመዝገብ ጀምረን ነበር። ነገር ግን አሁን በተደረገው ለውጥ የተወሰነ መንገጫገጭ በራስ መተማመን ተጫዋቾች እንዲያጡ አሰልጣኞቹ ደግሞ እንደ አዲስ ተረክበው ቡድኑን ለመስራት ጊዜ ማነስ እንደዚህ አይነት ውድድር ላይ ዋጋ አስከፍሉናል።

ከአንቺ የእረዳቱችሽ የአሰልጣኝ ስብስብ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ለውጥ ተደርጉበታ ተጫዋቾች ላይስ ምን ያህል ለውጥ ተደርግዋል?

እኔም እያለሁ በተወሰነ መልኩ ለውጡች ነበሩ ነገር ግን እያሳደግን ነበር የመጣነው እኔ በነበርኩበት ቤሔራዊ ቡድን የተለየ ነገር ሰራን ብዬ የምኩፈስበት ባይሆንም በነበረኝ ጊዜ በእግር ኳሱ የተወሰነ ለውጥ ለማምጣት ሙክርያለሁ የራሴን አሻራ ለመጣል። በመጀመሪያ ሴካፋ 3ኛ የወጣው ላይ ከዚህ ቀደም አስራ ሁለት አስራ ሦስት ዓመታትን የተጫወቱ ተጫዋቾች ነበሩ ሰለዚህ እነዚህ ተጫዋቾች አሁን በመጡ ተጫዋቾች መቀየር የመጀመሪያ ስራዬ ነበር ይህንንም ስደርግ ለውጡቹ ላይ የተወሰነ መንገጫገጭ ነበር ነገር ግን ቡድኑ በሂደት እየጠራ እየጠራ መጥቱ በኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ላይ ምንም ፍርሀት የማይሰማው ጠንካራ ቡድን ለመሆን ችሎ ነበር። ወደ መጨረ አካባቢ ላይ ውጤት የምናመጣበት ነው ብዬ አስብ ነበር ያው ፌዴሬሽኑ የራሱ ሀሳብ ይኖረዋል በዝያ ምክንያት ልውጥ አድርጓል ።በነዚህ ጊዜያት ግን ቤሔራዊ ቡድኑ እያደገ መሄዱ ቡዙ ማረጋገጫ አሉ የነበሩ ውጤቶች፣የተጫዋቾች የእድሜ ደረጃ ፣ ከዚህ በኃላ ስንት ዓመት ያገለግላል ፣በፊፋ በሚያወጣው ደረጃ ላይ መግባታችን እና 7 ደረጃዎችን ማሻሻላችን፣ የተለያዩ ሽልማቱችን ማግኝታችን በውድድሩ ላይ ምርጥ ቡድን ሆኑ ተሸልሟል በዝህ ውስጥ እያለፈ የመጣ ቡድን ነበር።ቅድም እንዳልኩህ አሰልጣኝ ሲቀየር እንዳአዲስ ቡድኑን የመላመድ ችግር ይገጥመዋል።አሁንም ቤሔራዊ ቡድኑ የገጠመው ችግር ከዚህ ውስጥ አንዱ ነው ማለት ነው።

ሁልጊዜ አሰልጣኞች በተቀያየረ ቁጥር እንደ አዲስ መስራት ምንድን ነው ምክንያቱ።

ምን መሰለክ ሀሳብ አይሸጋገርም ተጫዋቾች አይሸጋገሩም ሁሉም ነገር ይቁም እና እንደ አዲስ ይጀመራል ይህ በእግር ኳሱ ብቻ ሳይሆን በሀገራዊ ሲስተም ውስጥ የሚታይ ችግር ነው። ሀሳቡ ባይከፋም የሚያጣቸው ነገሩች አሉ መነሻ ሀስቦች የሚሆን በመረጃ ለፌዴሬሽኑ ሰጥቻለሁ። የተጫዋቾችን መረጃ ፣ ምን ያህል ተጫውተዋል ፣ ተፅዕኖቸው ምን ያህል ነው ከመጨረሻዎቹ ቀኑች ውጪ ከ17 ዓመት እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ለመረጃ ይጠቅማል ብዬ ለፌዴሬሽኑ አቅርቢያለሁ።በየጊዜውም የማደርጋቸው ሪፖርቱችም አሉ ሰለዚህ በቀላሉ አሰልጣኝ ብርሃኑ ከዝያ ማግኘት ይችል ነበር።ይህን ስል አሰልጣኝ ብርሃኑ ተጫዋቾችን አይቃቸውም የሚል ግምት የለኝም ።ነገር ግን ለሱ አስተሳሰብ ይሆኑኛል የሚላቸው ላይ ልዩነት ነበረን እኔ የማየው እንደዝያ ነው።አሁንም ቤሔራዊ ቡድኑ ላይ እርዳታ ለማድረግ በቀናነት ሙክርያለሁ። የሽግግር ላይ ይህ ነገር እስካለ ድረስ አሁንም ይቀጥላል አሁንም ሌላ አሰልጣኝ ቢመጣም እንደዚሁ ነው የሚሆነው። የኔ የሰራውት ቡድን ላይ ቲኒሽ ልጃች ናቸው ለውደፊት ብዙ የሚጫወቱ ናቸው ለኔ ቡድን አልነበረም ስሰራ የነበረው ለሲስተሙ ነበር። ወደ 8 ልጃች ከ17 ዓመት ቤሔራዊ ቡድን ሲጫወቱ የነበሩ ናቸው ወደ 12 ልጃች ከ20 ዓመት ቤሔራዊ ቡድን የነበሩ እና 3 ሲኒየር ተጫዋቾች የቀላቀልነው ይህ ምን ያሳያል ቀጣይ ትልቅ ቦታ ማድረስ ይቻላል የሚል ሀሳቡ ነበረን። ሰለዚህ በሚፈርስ ቡድኑ ውስጥ የምናጣቸው ነገሩች መፈጠሩ ልንገነዘብ ይገባል አሁን የማስበው ምንድን ነው ለአሰልጣኝም ለተጫዋቾችም ጊዜ ያስፈልጋል ምን እንደሚሰራ ለማወቅ ማለት ነው።

ወደ ቤሔራዊ ቡድን ስትመጪ ፌዴሬሽኑ ምን እንድታሳኩ ነበር ? ስትባረሪስ ምክንያታቸው ምንድን ነው?

ከ17 ዓመት ቤሔራዊ ቡድን ሲሰጠኝ ፌዴሬሽኑ ከኔ ምንድን ነው የሚፈልገው በኔ ምንድን ነው ሊያሳካ የሚፈልገው የሚል ነበር ጥያቄ ። በጊዜውየተሰጠኝ መልስ ማንም ሰው እንደሚሰራው ዝም ብለሽ ስሪ የሚል ነበር። ሰለዚህ ለራሴ ግብ አስቀመጥኩ ይህ ቤሔራዊ ቡድን ከዚህ ተነስቱ እዝህ መድረስ አለበት የሚል በእርግጠኝነት ይህ ነገር ባይፈጠር ኖሮ በሁለት አመት የአፍሪካ ዋንጫ በአራት ዓመት ውስጥ የአለም ዋንጫ ማሳካት የሚችል ግብ ሳስቀምጥ የነበረው። በተወሰነ መንገድ እየሄድኩ ነበር በትክክለኛው መንገድ የተወሰነ ስህተት ድክመት እንደ ባለሙያ ቢኖርብኝም።ያው አንድ ቀጣሪ ስፈልግ ይቀጥርሀል ሲፈልግ ደሞ ያባርሃል የተወሰነ ብቃት ያንሰኛል እዝያ ላይ እየሰራው ጥሩ አሰልጣኝ ለመሆን መሞከር ነው።

የሦስት ወር ኮንትራት ተገቢ ነው ወይ እናንተስ እንደ እንደ አሰልጣኝ ለምን ትቀብሉታላቹ? ፌዴሬሽኑ ይህንን መንገድ የሚከተለው ምን ታስቡ ነው?

የመጀመሪያው የዝህ ጉዳይ ባለቤት ፌዴሬሽኑ ነው እኛማ ተቀጣሪ ነን አንድ ወርም ቢሰጠን አስር ወርም ቢሰጠን ቤሔራዊ ቡድኑ ውስጥ መግባት እንደ ትልቅ ስኬት ነው የምናየው። ጊዜ ቢሰጠን እና ውጤት እንድናመጣ ቢደረግ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ፌዴሬሽኑ ነው። ሰለዚህ ፌዴሬሽኑ ያንን አይፈልገውም ማለት ነው ማለት የገንዘብ ውጪ አለበት ብዙ ወጪ አለ እነሱ እነሱ ናቸው ቅድሚያ የሚሰጣቸው።ፌዴሬሽኑ ለሁለት ጨዋታ እንዴት አስር ወር ኮንትራት እሰጣለሁ ያላል ሰለዚህ እኔ ልስብ የምችለው ቤሔራዊ ቡድን ሳይሆን ውጤት ነው ማለት ነው ። ሁለት አመት ሲሰጥክ የመጀመሪያ ሙሉ በራስ የመተማመን ይኖርካል ከዝያ ስለቀጣይ ቤሔራዊ ቡድን ታስባልክ በዚህ ደሞ መጀመሪያ እግር ኳሱን ይጠቀማል ቀጥሉ ፌዴሽኑ ይጠቀማል። በእግር ኳስ በአቋራጭ እውቅናን ለማግኘት ሴቶች እግር ኳስ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው። ሁለት አመት ቢሰጠኝ ይህን ማድረግ እችል ነበት ስለገንዘቡ ችግር የለብኝም በነፃማ ልሰራ እችላለሁ። እግር ኳሱ ሀሳቦች ሉኖርቱ ይገባል አሁንም አሰልጣኝ ብርሃኑ ሦስት ወር ሲሙላው አዲስ ሀሳብ አዲስ ቡድን መቼ ነው ቡድን የምሰራው ? 

ፌዴሬሽኑ ምክንያቱ ምንድን ነው ኮንትራቱ አጭር ሲሆን?

ገንዘብ የለንም!! እርግጥ ነው ለውጥ ላይ ነበሩ ገንዘብ አልነበራቸውም ምክንያት ሊሆን የሚገባው ግን ገንዘብ እንዴት እናግኝ ነበር ።ምክንያቱም ብራንድ ነው ቤሔራዊ ቡድኑ አሁን የወንዶቹ ቤሔራዊ ቡድን ሲያሸንፍ ምን ያህል ደስታ እንደነበረ እይ ስለዚህ መሳርያችን ነው

ብራንድ የሆነ ቡድንን ከጎን መሆን የማይፈልግ የለም እና ገንዘብ የሚያገኘበት ዋንኛው መንገድ ቤሔራዊ ቡድኑ ነው በዚህ ባልኩት ጎዳይ ማርኬቲንጉ ስራዎች ቢሰራ የገንዘብ ችግር መቅረፍ ይቻላል።
ሌላው የአመለካከት ችግር ነው የቤሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቁጭ ብሉ ደሞዝ የሚቁጥር ነው የሚመስለው ጭንቀቱ ፣ጫናው ብዙ ሰው አይገባውም ሰለዚህ ሁሉም ገንዘቡች የሚመጡት በቤሔራዎ ቡድኑች ነው እዝህ ላይ ጥርት አድርገን ካልሰራን ገንዘብ የምናመጣበትን እየገደልን ነው ብዬ ነው የማስበው።

ቤሔራዊ ቡድኑ ከሴካፋ ከምድብ ወድቋል ከፊታችን ደሞ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አለ ምን መደረግ አለበት?

የመጀመሪያው ነገር እዝያ ኖርኩም አልኖርኩም ቡድኑ መቀጠል አለበት እድሜያቸው ይታያል ያላቸው ወቅታዊ ብቃት ይታያል ሁለት ሦስት ልጅ መቀየር ችግር የለውም ግን ቡድኑ እንደ ቡድኑ መቀጠል ነበረበት በጣም የለፋንባቸው ሁለት ዓመት ለሆቴል ገንዘብ አለ ፣ የትጥቅ ገንዘብ አለ ፣ የጉዞ ገንዘብ አለ ይህንን ሁሉ ነው መና እያደረግን ያለው ሰለዚህ ወጥ የሆነ ቤሔራዊ ቡድን መገንባት አለብን አንዱ አሰልጣኝ ሲባረር ሌላኛው ማስቀጠል የሚችልበት ሲስተም ቢኖር በእርግጠኝነት ይህንን የአፍርካ ዋንጫ መሳተፍ እንችላለን። 

በአሁኑ የሴካፋ የተሳተፈው ቤሔራዊ ቡድን የተጫዋች አጠቃቀም ምን ትያለሽ?

እኔ እንደ አሰልጣኝ የማስበው አሰልጣኝ ብርሃኑ ሁለት ነገሩችን አስቡ ነው ይህን ያደረገው።ያለው የሦስት ወር ውል ሰለሆነ ከዚህ በፊት የነበሩት ሰርካለም ጉቱ እና መዲና አወል ናቸው ሽታዬን ሲሳይን ይዙ ሲህድ ግን እኔ እንደ አሰልጣ የምገነዘበው ውጤት ነው ይህ ደሞ ውሎ ያመጣበት ተጽኖ ነው ብዬ ማስበው። ሁለተኛው ደግሞ ሁለተኛ ስራ አለው ቡድኑ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በዝያው መገንባት ነው የኔ ሀሳብ ይህ ነው። ዘጠኝ ልጃች ነው ይሄደው 7ቱ ቋሚ ተሰላፊ ናቸው ሰለዚህ ሙሉ ስነ-ልቦና ከፍ አድርጉ ለውድድሩ ይመለሳል።እንደ አሰልጣኝ ካየነው ልክ ነው እንደ እግር ኳስ ግን ልክ ነው ብዬ አላስብም።

አሰልጣኝ ሰላም አሁን ከቤሔራዊ ቡድንም ለቀሻል ከክለብም ለቀሻል አሁን በምን ሆኔታ ላይ ነሽ?

በአሰልጣኝነት ድክመት አለብኝ እሱ ላይ እየዘመትኩበት ነው በሚቀጥለው ወደ ስራ ማለቴ በአሰልጣኝነቱ ላይ ከድሩዋ ሰላም የተሻለ ሆኝ ለመመለስ በዝህ ላይ አሳልፋለሁ። 

በክለብም ሆነ በቤሔራዊ ቡድን ለመባረር ድክመቴ ምንድን ነው ትያለሽ ?

ስለያይ እንደ ተቀጣሪ ምክንያት ይኖራችዋል ብዬ ነው የማስበው። ሰለዚህ ያ ምክንያት ምንድን ነው ብዬ ለራሴ የማወጣቸው ድክመቱች አሉኝ ። ሁሉጊዜ ለሰዎች ጥንካሬን ለማሳየት ነው የምሙክረው እና ለራሴ ግን ብዙ ድክመቱች አሉኝ ለምሳሌ በስልጠናው ብዙ እርቀት መጓዝ አለብኝ ብዬ ካሰብኩ በቋንቋው እና ብዙ ማንበብ ይኖርብኛል በአሁን ሰዓት ደሞ ብሪቲሽ ካውንስል ተመዝግቤ እየተማርኩ እገኛለሁ ይህንን ከጨረስኩ የአረበኛ ቋንቋ እጀምራለሁ ለወደፊት ኢንተርናሽናል ስራ ይገጥመኛል ሰለዚህ ድክመቴ ላይ ነው እየሰራው ያለውት።

በቀጣይ ወንዶች ላይ የመስራት ሀሳብ አለሽ?

እኔ ደስ የሚለኝ እግር ኳሱ ላይ መሆኔ ላይ ነው አሁን በጣም ከባድ እየሆነ ያለው እግር ኳሱ ላይ ከፍተኛ ብር እየተዘዋወረ ስላለ ነው እኔ የምፈልገው በነፃ የምፈልገውን የምሰራበት ነፃነት ያለበት ቦታ ቢሆን እመኛለሁ። ያለፊት 9 አመት ቅ/ጊዮርጊስ ውስጥ ሦስት ሺ ብር ነበር ደሞዜ ገንዘብ ላይ አልነበረም ስሰራ የነበረው ወይም ገንዘብ አልነበረም አላማዬ በጣም ብዙ ማሳካት አለብኝ ብዬ ስለማስብ ነው እነኝህ 7 -9 አመታት ባከኑ ብዬ አላስብም በደንብ ተጠቂሜባችዋለሁ ድግሪ ይዥለሁ በስፖርት ሳይንስ ኤ ላይሰንስ ደርሻለሁ አሁን ኢንስትራክተር ሆኛለሁ ይህ ገና መነሻዬ ነው። ብዙ የማስባቸው አሉ እነሱ ቢሳኩልኝ ደስ ይለኛል።

በመጨረሻም ለእኔ አስደሳች እና አሳዛኝ የምትይው?

እኔ ጋር ብዙም የስሜት ለውጥ የለም አንድ አይነት ነው ። ነገር ግን በጣም የምናደደው ተጫዋቾች በተሳሳተ መልኩ የተረዱኝ ከመሰለኝ ማስረዳት አለመቻሌ ያናደኛል።በህይወት ደግሞ ማግኘት ሲኖርብክ ስታጣ ያው አዝናለሀ ይህ ነው፡፡


ሁለተኛ ሳምንት

ተጨማሪ

Wed 22 Jan 2020
የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ያግኙ
email