የ2012 የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ዛሬ የኢትዮጵያ ሴት እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ይፋ አድርግዋል፡፡

Thu 07 Nov 2019 Dawit Habet

ካሳለፉዎቸው ውሳኔዎች መካከል የ2012 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ህዳር 13 የዕጣማውጣት ስነ ስርዓት እንደሚካሄድ ሲገልፅ።


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ዲቪዚዮን ውድድር ህዳር 27 እንደሚጀመር እና  የ2ኛ ዲቪዚዮን ውድድር ደግሞ ታህሳስ 18 ሊጀመር እንደሚችል ገልፀዋል።በሌላ ውሳኔ የውድድር ደንቡ በኮሚቴው እንዲገመገም እና አሰሪ በሆነ መልኩ ማሻሻያ እንዲደረግበት ኮሚቴው ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን የ2012 የሴቶች

እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ በአንደኛ ዲቪዚዮን 12 ክለቦች እንዲሁም በሁለተኛ ዲቪዚዮን 9 ክለቦች የሚሳተፉ ይሆናል ተብሏል። 


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ ክለቡች እራሳቸውን እያገለሉ በሚገኘበት በዚህ ሰዓት በወ/ሮ ሶፊያ አልማሙ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ያለው ነገር አለመኖሩ  የክለቦችን መመናምን ሆነ የመፍረስ አደጋ እምብዛም ያላሳሰባቸው ጉዳይ መሆኑን በቂ ማሳያ ነው።ፎቶ ከኢእፌ ገፅ


ሁለተኛ ሳምንት

ተጨማሪ

Wed 22 Jan 2020
የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ያግኙ
email